| ወጣቱ በወያኔ አፈና ምክንያት ለስደት እየተዳረገ መሆኑ ታወቀ! |
|
|
|
| Written by Administrator |
| Saturday, 25 February 2012 08:36 |
|
የአገራችን ኢትዮጵያ ወጣት በተለይ ከምርጫ 97 ወዲህ ከፍተኛ እንግልት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፣ በአምባገነኑ አገዛዝ ሆድ አምላኪ ስግብግቦች የሀገርና የወገን ብልፅግና ሞተር የሆነው ወጣቱ ትውልድ በጎጠኛው ስርአት እንደጠላት ከመታየቱም በላይ የህዝቡን ኑሮ ለመስማት በሚያደርጋቸው የትኛውንም አይነት እንቅስቃሴ በህዝብ ደም በጠገቡ እብሪተኞች አናቱን በጥይት አረር ከመነደል አልዳነም፣ እንደሚታወቀው በጎንደር አካባቢ በከፍተኛ ሁኔታ የሚመረተው የማሽላና የሰሊጥ ምርት የጉልበት ስራ ለመስራት ከአራቱም አቅጣጫ የአገራችን ኢትዮጵያ ነዋሪዎች ወደዚህ አካባቢ በሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች እንደሚተሙ ይታወቃል፣ በጉልበት ስራ ራሳችንና ቤተሰባችንን እናሳድጋለን ብለው ከቀያቸው ወደ ሰሜኑ ክፍል ያመሩ ኢትዮጵያውያን አላማቸውን ለማሳካት ደፋ ቀና ቢሉም እንዃን የወያኔው ግብዝ አሸርጋጆች ጋሬጣ ሆኖባቸዋል፣ ከሱዳን ጠረፍ አካባቢ በጉልበት ስራ ይተዳደሩ የነበሩና ገና ስራ በመፈለግ ላይ የነበሩ ወጣቶች ገሚሶቹ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን ልትቀላቀሉ አስባችዃል ከዚህ ቀደም በፀረ-ኢህአዴግ ትግል ውስጥም ተሳታፊ ነበራችሁ በማለትና አገራችን በከፍተኛ ሁኔታ በለውጥ ጎደና እየተጓዘች ባለችበት አካኋን ወደ ሱዳን ልትሰደዱ አስባችኋል እየተባሉ በቋራ መተማ አርማጭሆና ሁመራ በመሳሰሉ አካባቢዎች ላይ በዛው አካባቢ ተወልደው ላደጉ ወጣቶችና የጉልበት ስራ ሰርተው የሚያገኟትን ገንዘብ ቋጥረው ወደ መጡበት ለመመለስ አስበው የነበሩ ወጣቶች ሃሳባቸውን ሳያሳኩ በጎጠኛው አገዛዝ ተላላኪዎች አፈሳ መለስና ግብረአበሮቹ አውርተው የማይጠግቡት የአባይ ግድብ ግንባታ እየተካሄደለት ነው በሚባለው የቤንሻንጉል አካባቢ በመውረድ በወያኔው የጦር ሃይል ጥበቃ በመሳሪያ ተከቦ በነፃ እንዲያገለግል እየተደረገ ይገኛል፣ ከዚህ አፈሳ በለስ ቀንቷቸው የተረፉ የጉልበት ሰራተኞችን በጎጥና በመንደር እያደራጀ እርስ በእርስ እንዲጫረሱ የጥላቻና የብተና ፖለቲካን ለመንዛት በጠላትነት እንዲተያዩ ከማድረጉም በላይ እርስ በእርስ እንዲደባደቡ ብሎም እንዲገዳደሉ መደረጉ ይታወቃል፣ ይህ ከኢትዮጵያዊነት ታሪክ አንፃር እጅግ የሚቃረን ድርጊት በህዝቡ ላይ ለመፈፀም አገዛዙ ለአንዴም እንዃን በስህተት በጉዳዩ ዙሪያ የማጣራት፤ የማርገብና ጥፋተኛን አግባብተው የማስተካከያ እርምጃ ወስዶ ገፅታውን መቀየር ሲገባቸው በየወቅቱ ለሚፈጠሩ ክስተቶች ላይ ቤንዚን ለማርከፍከፍ የበለጠ ግጭቱ እንዲፋፋም መሳሪያ ሲያቅብል እንደነበር ሲታወቅ ዛሬ በተቃራኒው ወጣቱ በፀረ-ወያኔ ትግሉ መስክ መስማማት ሲያይል ጉዳዩ ያሰጋው እብሪተኛው ስርዓት በጉልበት ስራ በአካባቢው የሚተዳደሩ ወጣቶችን እናስማማለን የሚል የይስሙላ ጥሪ እያቀረበ ይገኛል፣ ሁኔታውን በአንክሮ ይከታተሉ የነበሩ ወገኖች እንዳሳሰቡት አሁን ላይ እናስታርቃችሁ እናስማማችሁ የሚል የይስሙላ ጥሪ ያቀረበው እውነትም ለማስማማት ሳይሆን በወጣቱ ዘንድ እየጠነከረ የመጣው አብሮኝነት ለመበታተን እንደሆነና ከሰራተኞች ውስጥ የኢህአዴግ አባላት ፎርም ለማስሞላት በውስጣቸው እየተከናወኑ ለሚገኙ አስጊ ጥረቶችን የተወሰኑ ለገንዘብ ያደሩ ተላላኪዎችን እንደተለመደው ለመመልመል እንደሆነ ያስረዳሉ፣ በሌላ ዜና በታች አርማጭሆ ጫንቃ በቅርቡ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት ከወያኔው ልዩ ሃይል ተብየ ታጣቂ ጋር ባደረገው ውጊያ 3 (ሶስት) የልዩ ሃይል ወታደሮችን ገድሎ 8 (ስምንት) በማቁሰል ድል እንደተቀዳጅ ይታወቃል፣ ተልዕኮውን በአግባቡ የተወጡት የኢሕአግ ሠራዊት አባላት ከወታደራዊ ጥቃቱ ጎን ለጎን አገዛዙ የሕዝቡን የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየር እያደረጋቸው በሚገኝ ውዥንብሮች ሳይዘናጋ ለአንድነትና ለዴሞክራሲ እየተደረገ ያለውን ሁሉ አቀፍ አገራዊ ትግል ማገዝ የውዴታ ግዴታችን ነው ላሉ በሰሜ ጎንደርና አካባቢው በሚገኙ የተለያዩ የማህበረሰብ አካላት ማለትም ለአርሶ አደሩ፤ ለተማሪው፤ ለመንግስት ሰራተኛው፤ ለጉልበት ሰራተኛው ብሎም ለመሳሰሉት በመሰብሰብ ትምህርት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፣ በተሰጣቸው ትምህርትና በአካባቢው አርበኛው በሚያደርገው ተጋድሎ ከፍተኛ ኩራት የተሰማቸው ኢትዮጵያዊያን አገዛዙን በጠበንጃ አፈሙዝ ለመጋፈጥ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን ሠራዊት እየተቀላቀሉ እንደሚገኙ የሰራዊት አመራር አባላት ከስፍራው ካስታወቁ በኋላ በመጨረሻም ግንባሩ በጎጠኛው ስርዓት ላይ እየሰነዘረ በሚገኘው ጥቃት ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ ተሳታፊ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል፣ |
Search
Latest Articles
-
10-09-2005
(1999-11-30 00:00:00) -
08-09-2005
(1999-11-30 00:00:00) -
06-09-2005
(1999-11-30 00:00:00) -
03-09-2005
(1999-11-30 00:00:00) -
01-09-2005
(1999-11-30 00:00:00)





