| ሰሜን ጐንደር |
|
|
|
| Written by Administrator |
| Thursday, 26 July 2012 01:36 |
|
የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ወታደራዊ ጥቃት ፈፀመ የግፍ አገዛዙንና ነፍጥ አምላኪውን የወያኔን ስርአት ለማስወገድ ቆርጦ የተነሳው የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት የተሰለፈበትን ወታደራዊ ግዳጅ አጠናክሮ በመቀጠል አንፀባራቂ የሆኑ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ድሎችን በማስመዝገብ ላይ እንደሚገኝ የግንባሩ ወታደራዊ መምሪያ ሰሞኑን በላከው መረጃ አመለከተ። የአትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ወታደራዊ መምሪያ ሰሞኑን በላከው መረጃ አንደገለፀው ሐምሌ 8 ቀን 2004 ዓ/ም ሰሜን ጐንደር ሶሮቃ ልዩ ስሙ ጯሒት በተባለ ቦታ የግንባሩ ሰራዊት በወሰደው ድንገተኛ ማጥቃት 3 የጠላት ወታደሮችን ገድሎ 5 በማቁሰል እንዲሁም የተለያዩ መሳሪያዎችንና ወታደራዊ ትጥቆችን በመማረክ የግንባሩ ሰራዊት አንፀባራቂ ድል ማስመዝገብ እንደቻለ የኢህአግ ወታደራዊ መምሪያ ባደረሰን ዘገባ ለማወቅ ተችሏል። የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ወታደራዊ መምሪያ ጨመሮ እንደገለፀው በአሁኑ ሰዓት በጐንደር አካባቢ እየታየ ያለውን የህዝብ መነሳሳትና የአልገዛም ባይነት ስሜትን በሃይልና በጫና ለማፈን የወያኔ ስርአት ከወትሮው በተለየ ሁኔታ በከባድ የጦር መሳሪያ የታጀበ ብዛት ያለውን የጦር ሰራዊት በአካባቢው በማሰማራት አገዛዙ በአካባቢው ማኅበረሰብ ላይ እየፈፀመ ያለው በደልና ሰቆቃ ከመቼውም ጊዜ በላይ የከፋ መሆኑን የግንባሩ ወታደራዊ መምሪያ የላከው ዘገባ ያስረዳል። የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በቅርቡ የዋልድባ ገዳምን ለማፍረስ የተሰማሩ የወያኔ ቡል ዶዘሮችን ሙሉ በሙሉ ማውደሙን ተከትሎ የወያኔ ቡድንም በበኩሉ በየወቅቱ በኢህአግ ሰራዊት እየደረሰበት ያለውን ወታደራዊ ጥቃት ለመመከትና ለመከላከል ወያኔ ተጨማሪ ጦሩን ከመሀል አገር እያነሳ ወደ አካባቢው እያሰፈረ ቢሆንም ከኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ተደጋጋሚ የጥቃት እርምጃ ሊያመልጥ አልቻለም። በዚህ መሰረት በሰሜን ጐንደርና በአካባቢው ተሰማርቶ የአካባቢውን ህዝብ ሲያሸብርና ሲያስፈራራ የነበረው የወያኔው ቅጥረኛ ሰራዊት በሐምሌ 8 ቀን 2004 ዓ/ም በኢህአግ ሰራዊት የተቃጣበትን ወታደራዊ ቅጣት መመከት ተስኖት ሙትና ቁስለኛውን ጥሎ እግሬ አውጭኝ በማለት ለመሸሽ እንደተገደደ የግንባሩ ወታደራዊ መምሪያ ከስፍራው በላከው ዘገባ አስታውቋል። የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ወታደራዊ መምሪያ ጨምሮ እንደገለፀው በአካባቢው ተሰማርቶ የሚገኘው የወያኔ ጦር የውጊያ ዝግጅቱንም ሆነ የውጊያ ሞራሉ የላሸቀ ከመሆኑም በላይ ከአርበኞች ግንባር ሰራዊት የሚሰነዘርበትን ድንገተኛ ማጥቃት የሚከላከለው በደመ-ነፍስና በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ብቻ በመሆኑ የግንባሩ ስራዊት ቀጣይ በሚፈፅማቸው ወታደራዊ ኦፕሬሽኖች በቀላል መስዋትነት አንፀባራቂ ድልን ማስመዝገብ የሚቻልበት ወቅት ላይ ተደርሷል በማለት የግንባሩ ወታደራዊ መምሪያ በዘገባው ጨምሮ ገልፆል። እንደሚታወቀው ባለፈው ወር መጨረሻ አካባቢ ከ40 በላይ የሚሆኑ የወያኔ መከላከያ ሰራዊት አባላት ከአሁን በኋላ በህዝባችን ላይ ግፍ ለመፈፀምም ሆነ ከአርበኞች ግንባር ሰራዊት ጋር ለመዋጋት ፍላጎት እንደሌላቸው በአሳዩት ቁርጠኛ አቋም የተነሳ የወያኔው ቡድን በበኩሉ እነዚህን የመከላከያ ሰራዊት አባላት ትጥቃቸውን አስፈትቶ ወደ እስር ቤት የላካቸው መሆኑን በወቅቱ መዘገባችን የሚታወስ ነው። |
Search
Latest Articles
-
10-09-2005
(1999-11-30 00:00:00) -
08-09-2005
(1999-11-30 00:00:00) -
06-09-2005
(1999-11-30 00:00:00) -
03-09-2005
(1999-11-30 00:00:00) -
01-09-2005
(1999-11-30 00:00:00)




