company logo

የራዲዮ ፕሮግራም

Content View Hits : 134359
Home ዜና በአርማጭሆ ወታደራዊ ጥቃት ፈፀመ
በአርማጭሆ ወታደራዊ ጥቃት ፈፀመ PDF Print E-mail
Written by Administrator   
Thursday, 09 August 2012 16:58

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በአርማጭሆ ወታደራዊ ጥቃት ፈፀመ።

    ኢሕአግ በሰሜን ጎንደር አርማጭሆ ልዩ ስሙ አዋሳ በተሰኘ አካባቢ ከወያኔው ልዩ ሃይል ታጣቂ ጋር በሐምሌ 28-2004 ዓ∙ም በተካሄደ ውጊያ 11(አስራ አንድ) የአናሳው ቡድን ቅጥረኞችን በመግደልና 19(አስራ ዘጠኝ) በማቁሰል አንፀባራቂ ድል ተጎናፀፈ።

  የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር የኢትዮጵያውያን መነጋገሪያ የሆነው የለገሰ ዜናዊ ጉዳይ በሚናፈሰበት በአሁኑ ወቅት ድርጅቱ በእብሪተኛው አገዛዝ የሃይል ጣቢያዎች ላይ የሚሰነዝራቸው ጥቃት አየጎለበተ ይገኛል።

  በእለቱ የግንባሩ ጀግና ሰራዊት የተለመደውን ታሪካዊ ጀብድ ሲያከናውን የአካባቢው ማህበረሰብ ከፍተኛ ድጋፍና አቀባበልም አድርጓል። ማህበረሰቡ የአርበኛ ግንባር ደጋፊ ነህ በሚል ሳቢያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሰነዘረበት ያለው የግፍ በትር እያየለ መምጣቱ ይታወቃል። በአካባቢው በኢንቨስትመንት ሽፋን አገሬውን በማፈናቀልና እርስት አልባ በማስቀረት በኩል አገዛዙም የበቀል እርምጃም እየወሰደ ይገኛል።

  የሙስሊሙ ማህበረሰብ በህገ-መንግስቱ የተቀመጠውና ሃይማኖትና መንግስት የተለያዩ ስለመሆናቸው የሚያትተው አንቀፅ ተግባራዊ ለምን አልሆነም በሚል በመላው አገራት የሚገኙ የሙስሊም ሃይማኖት ተከታዮችና ህዝበ ክርስቲያኑም ጭምር ቁጣ መቀስቀሱ ይታወቃል፡

   ይህ ከሃይማኖት ጋር የተጣላ የወንበዴ ቡደን ስለ እውነት የተናገሩ አለያም የፃፉ የፖለቲካ ሰዎች ጋዜጦችና በተለያየ ስራ የሚተዳደሩ ዜጎችን ያለ አግባብ ለእስር በመዳረግ አገሪቷንና ህዝቦቿን መቀመቅ ለመክተት እየባዘነ የሚገኘውን አሸባሪ ቡድን ፊት ለፊት በጠመንጃ አፈሙዝ በመፋለም ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በሰሜኑ ክፍል እያካሄደው በሚገኘው ድንገተኛ ወታደራዊ ጥቃት ድል እየተቀዳጀ መምጣቱ የሚታወቅ ነው።

  ግንባሩ እየወሰዳቸው በሚገኝ ወታደራዊ ጥቃቶች ጎን ለጎን እንደ ወትሮው ሁሉ ህዝቡን የማንቃትና የማስታጠቅ እንዲሁም የድርጅቱ አቋም ገላጭ የሆኑ በራሪ ወረቀቶችና መፅሔትቶች ተሰራጭተዋል። በሰራዊቱ በኩል እየተወሰደ በሚገኘው አገርን ከጥፋት ሃይሎች የመታደግ ታሪካዊ እንቅስቃሴ አንጀቱ የራሰው ምስኪኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዛሬም ለለውጥ የሚያደርገውን ትግል ማጠንከር እንደሚገባውና ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ወቅት ሊፈጠሩ ይችላሉ በሚባሉ መላ-ምቶች ሳንዘናጋ የኢሕአግ ሰራዊት እየወሰዳቸው ባሉ ወታደራዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ኢትዮጵያዊ የሆነ ወይም የኢትዮጵያ ጉዳይ ይመለከተኛል ያገባኛል የምንል ወገኖች ሁሉ በአረመኔውና ጨካኙ የወያኔው ቡድን ላይ የምንረባረብበት ወቅት አሁን ነው ሲሉ በታች አርማጭሆ ልዩ ስሙ አዋሳ በተሰኘ ቦታ ላይ የአገዛዙን ቅጥረኛ ሰራዊት አይቀጡ ቅጣት ከቀጡት የጦሩ አመራር አስታውቀዋል።

      በሰሜን ጎንደር የሚገኘው የወያኔው ልዩ ሃይል ታጣቂ ቡድን ዘረፋና ነጠቃ መጀመሩ ታወቀ።

   የአርበኛውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ለማክሰም በሚል አላማ የተደራጀው የልዩ ሃይል የሚባለው ታጣቂ የወያኔ የበላይ የጦር መኮንኖች ሃይሉን ካደራጁበት በተቃረነ መልኩ ለሕዝብና ለሀገር ብልፅግና ሲባል ተደራጀ የተባለው ታጣቂ ቡድን በቀን በጠራራ ፀሐይ ከወልቃይት ሶረቃ አንስቶ በአርማጭሆና መተማ አይን ያወጣ ዘረፋ የጀመሩ ሲሆን ዘረፋው የሕዝብ መገልገያ በሆኑ አውቶቡሶችና አገር ሰላም ነው ብለው ከቦታ ቦታ በሚንቀሳቀሱ ዜጎች ላይ ያነጣጠረ መሆንና ሕዝቡም የሕግ ያለህ ጩኸቱን እያሰማ ከመገኘቱም በላይ ሕግ አስከባሪ በተባሉ ሃይሎች እድሜ ልካችንን የለፋንበትን ሀብት እንዴት እንነጠቃለን የሚልና ይህ የሚያሳየው በአንድ አገዛዝ ውድቀት ወቅት ይከሰት የነበረውን ዘረፋና ግርግር ያስታውሰናል ካሉ በኋላ ስርዓቱ በሕይወት ስለመኖሩ የሚያጠራጥር ሆኖ አግኝተነዋል ያሉ ሲሆን፣ የዘረፋው ሰለባ የነበሩ ወገኖች እንዳስታወቁት ሂደቱ የሚያሳየው ወያኔ መውደቂያው የተቃረበ በመሆኑ ሁላችንም የየበኩላችንን መንትፈን እንሰወር የሚል መልዕክት እንዳለው መገመት አይከብድም ብለዋል።

  የልዩ ሃይል ታጣቂ አባላት በዚህ ሳምንት ውስጥ የጀመሩት አይን ያወጣ ዘረፋ ይህ መረጃ ይፋ እስከተደረገበት ዕለት ድረስ ያልተቋረጠ እንደሆነ የአካባቢው ነዋሪዎች በምሬት አስታውቀዋል።

                                                          

 

Search

Latest Articles

  1. 10-09-2005
    (1999-11-30 00:00:00)
  2. 08-09-2005
    (1999-11-30 00:00:00)
  3. 06-09-2005
    (1999-11-30 00:00:00)
  4. 03-09-2005
    (1999-11-30 00:00:00)
  5. 01-09-2005
    (1999-11-30 00:00:00)



Copy right @2010 arbegnochginbar