company logo

የራዲዮ ፕሮግራም

Content View Hits : 135638
Home ስለ ኢሕአግ
ከኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር የተሰጠ መግለጫ - Page 2 PDF Print E-mail
Written by Administrator   
Wednesday, 07 April 2010 18:19
Article Index
ከኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር የተሰጠ መግለጫ
Page 2
All Pages

 

 

 

 

 

Email – This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it website- www.arbegnochginbar.com

 

logoየኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ከተመሰረተ አንስቶ አገርን የማዳን አኩሪ ተግባራትን በተለያየ መስክ ያደረገ ሲሆን፣ ከዚህ በላቀና በተደራጀ መልኩ በግንባሩና በአለም አቀፍ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን አገርና ህዝብን ለመታደግ በሚደረገው ትግል ካለፉት አመታት የበለጠና የተጠናከረ ህዝብ አቀፍ ስራ ለመስራት ከመጋቢት 22 እስከ 25/ 2002 አ.ም በተካሄደው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ መሰረት ቀጥሏል።

የኢህአግ ሰራዊት በወያኔ ላይ እየወሰደ ያለውን ወታደራዊ የማጥቃት እርምጃ ከእስካሁኑ በላቀ ሁኔታ ወያኔው የሚመካበትን የታጠቀ የግፍ ሃይል ለማንኮታኮት እየሰራ ይገኛል።

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወያኔን ለማስወገድ በሚካሄደው እንቅስቃሴ ቀላል የማይባል ሚና ተጫውተዋል። ይሁን እንጅ ተሳትፉቸውንና ጥረታቸውን በማዋሃድና አንድ አቅጣጫ በማስያዝ ረገድ በርካታ ሙከራዎች የተደረጉ ቢሆንም የተፈለገውን ያህል ውጤት አላስገኘም። ድርጃታችን ኢ.ህ.አ.ግ ይህን በመረዳት ከውጭ በተመረጡ ማእከላዊ ኮሚቴ አባላትና ከነሱም መካከል በሰብሳቢው በምክትል ሰብሳቢው እና በዋና ፀሃፊው አስተባባሪነትና አመራር ሰጭነት ሲሆን 14ቱ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላትና ሌሎች ነዋሪነታቸውን በውጭ ያደረጉ ወገኖች ሁሉ በተመቻቸው አንድ ወጥ መንገድ ስር በመሰባሰብ እና የሚሰጠውን አገራዊ ተልእኮ በመፈፀምና በማስፈፀም አገርና ህዝብን እያወደመ የሚገኘውን አንባገነኑን የወያኔ ቡድን ይበቃል ልንለው ይገባል። በተለያየ መንገድ በኢ.ህ.አ.ግ ስም ይንቀሳቀሱ የነበሩ ቡድኖች ህዝብን ከማወናበድ ተግባር ተቆጥበው በተመቻቸው መንገድ ውስጥ ገብተው እንዲንቀሳቀሱና በጉባኤው በተላለፈው ውሳኔ መሰረት arbegnochginbar.com ውጭ በኢህአግ ስም የተከፈቱ ድረ- ገፆች ህገ-ወጥ መሆናቸውን እያሳወቅን ድርጅታችን በወታደራዊ በፖለቲካና በዲፕሎማሲ… ያለውን ሃይል በመጠቀም ተግቶ ይሰራል።

ወያኔው እየተዘጋጀለት የሚገኘውን የይስሙላ ምርጫ ምእራባውያንም ቢሆኑ እውነታውን የተገነዘቡበትና ፊታቸውን ያዞሩበት ወቀት በመሆኑ በዚህ አጋጣሚ ኢትዮጵያዊ የሆንን ወገኖች ሁሉ ጎጠኛውን አገዛዝ ከስር መሰረቱ ለማስወገድ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር አንድ አካል ሆነን አገራችን ኢትዮጵያን ከገባችበት አዘቅት ልናወጣት ይገባል።

አንድነት ሃይል ነው!!!

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር

መጋቢት 20 ቀን 2002 አ/ም



Last Updated on Friday, 11 March 2011 14:20
 

Search

Latest Articles

  1. 10-09-2005
    (1999-11-30 00:00:00)
  2. 08-09-2005
    (1999-11-30 00:00:00)
  3. 06-09-2005
    (1999-11-30 00:00:00)
  4. 03-09-2005
    (1999-11-30 00:00:00)
  5. 01-09-2005
    (1999-11-30 00:00:00)



Copy right @2010 arbegnochginbar