|
Written by Administrator
|
|
Tuesday, 07 May 2013 15:19 |
|
የኢሕአግ የቻፕተር ኮሚቴዎች ድጋፍ እያደረጉ ነው።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በተለያዩ የአለም ሃገራት የሚገኙ የድጋፍ ኮሚቴ ቻፕተሮች ድጋፍ ማድረግ መጀመራቸውን የድርጅቱ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ አስታወቀ።
ድርጅታችን ከአሁን በፊት ባካሄደው ኮንፈረንስ ላይ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት በየሀገራቱ ቻፕተሮች ተቋቁመው ተጠሪነታቸው ከድርጅቱ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ጋር መሆኑ የሚታወስ ሲሆን፣ በዚህም መሰረት እስከአሁን በጀርመን፣ በአውስትራሊያ፣ በኖርዎይ፣ በስዊድን ፣ በቤልጅየም፣ በካናዳ ተደራጅተው እንቅስቃሴ መጀመራቸው ይታወሳል።
|
|
Read more...
|
|
|
Written by Administrator
|
|
Tuesday, 30 April 2013 08:24 |
|
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ወታደራዊ ጥቃት ተጠናክሮ ቀጥሏል::
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞ ግንባር ሰራዊት ድንገተኛ ወታደራዊ ጥቃት ከቀናት በፊት በዋልድባ ሰቋርና አምቦ ጠበል ለሁለት ቀን ባደረገው ውጊያ 46 ገድሎ 64 ማቁሰሉን መዘገባችን ይታወቃል።
ጥቃቱ እንቅስቃሴውን በማስፋት በሚያዚያ 15-2005 ዓ.ም ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ከወያኔው ፈጥኖ ደራሽ ሐይልና ከፌደራል ጋር በተካሔደው ውጊያ በወረዳ አድርቃይ ልዩ ስሙ አሌ በተባለው ቦታ 17 የጠላት ቅጥረኞችን በመግደልና 24 በማቁሰል ከፍተኛ ድል ተቀዳጅቷል።
|
|
Read more...
|
|
Written by Administrator
|
|
Monday, 22 April 2013 16:09 |
|
ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር /ኢ.ሕ.አ.ግ/
የተሰጠ መግለጫ
የኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪክና ማንነቱን ስንመረምር ሁሌም አስቀድሞ የሚታየን አትንኩኝ ባይነቱ ፣ ታጋሽነቱ፣ ብልሕና አስተዋይነቱ እንዲሁም ጀግንነቱ መቼም ቢሆን ከሕሊናችን የማይሰወር እውነታ ነው።
ይህ ኩሩና ጀግና ሕዝብ ላለፉት 21 ዓመታት ማንነቱን የሚፈታተኑ ኢ- ሰብዓዊና ኢ-ሞራላዊ የሆኑ አስከፊ ግፍና መከራን በሀይል እንዲቀበል አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ ከመፈተን ለአንድም ደቂቃ ቢሆን ቦዝኖ አያውቅም።
የአካባቢ ምርጫ እየተባለ ለይምሰል ሁነኛ ተወዳዳሪ በሌለበትና የፖለቲካ ምሕዳር በጠበበት ሁኔታ ለግሉ በተቆጣጠረው ሚዲያ ለብቻው ተራ ድስኩር በሚያስተጋባበት በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር አገር አድን ሰራዊት በሚያዚያ 8ና በሚያዚያ 9-2005 ዓ.ም ታሪካዊውን የዋልድባ ገዳም ለማፍረስ ታች ላይ እያሉ በሚገኙ ሰራተኞች ጥብቃ እየተደረገ ከሚገኘው ከአገዛዙ የመከላከያ ሰራዊት ተመርጠው ከተውጣጡ የፈጥኖ ደራሽ ታጣቂ ሃይሎች ጋር ለ2 ቀን ባካሔደው ከፍተኛ ውጊያ የጠላትን አንገት ያስደፋ በአንጻሩ ወገንን ያኮራ ድል መቀዳጀቱ ይታወቃል።
|
|
Read more...
|
|
|
የኢሕአግ ሰራዊት በዋልድባ ወታደራዊ ጥቃት ፈፀመ |
|
|
|
|
Written by Administrator
|
|
Thursday, 18 April 2013 09:02 |
|
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በዋልድባ አካባቢ ልዩ ስሙ ሰቋር እና አምቦ ጠበል በተባለ ቦታ በተከታታይ ሁለት ቀናት ከወያኔው የፈጥኖ ደራሽ ጋር ባደረገው የፊት ለፊት ውጊያ በጠላት ላይ ወታደራዊ የበላይነትን በመቀዳጀት አኩሪ የአርበኝነት ጀብድ ፈፅሟል።
የግንባሩ ሰራዊት በዋልድባ ልዩ ስሙ ሰቋር በተባለ ቦታ በሚያዚያ 8-2005 ዓ.ም የወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ መመኪያ በሆነው የፈጥኖ ደራሽ ላይ በከፈተው የማጥቃት እርምጃ 21 የጠላት ወታደሮችን በመግደል 25 ያቆሰለ ሲሆን፣ በተመሳሳይ በሚያዚያ 9-2005 ዓ.ም በዋልድባ ልዩ ስሙ አምቦ ጠበል በተባለው ቦታ ውጊያው የተካሄደ ሲሆን በዚሁ እለትም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት 25 የጠላት ወታደሮችን ገድሎ 39 በማቁሰል ከፍተኛ ድል የተቀዳጀ ሲሆን፣ በዚሁ አውደ-ውጊያ ላይም የተለያዩ የቡድንና የነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያዎችንም ከመሰል ጥይቶቻቸው ጋር ማርኳል።
|
|
Read more...
|
|
Written by Administrator
|
|
Wednesday, 27 February 2013 05:27 |
|
በሰሜን ጎንደር መተማና አካባቢው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በራሪ ወረቀት በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ ሲሆን ፣ የወያኔ ካድሬዎችም ድርጊቱን ለማስቆም የተጠናከረ አሰሳ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በመላ ሀገሪቱ እየታየ ያለው የሕዝብ መነሳሳት ስሜትና ተጋድሎ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከለውጥ ፈላጊው ሕዝብ ጎን የቆመ መሆኑን በተለያዩ ጊዜያቶች በጠላት ላይ በሚያደርሰው ጥቃት የሀገርና የወገን ደራሽነቱን ያስመሰከረ ሲሆን፣ ከወታደራዊ ትግሉ ጎን ለጎን የአካባቢውን ህብረተሰብ የማስተማር፣ የመቀስቀስ፣ የማደራጀትና የማስታጠቅ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ተገለፀ።
በሰሜን ጎንደር መተማና አካባቢው በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኛች ግንባር ደጋፊዎች አማካኝነት የድርጅቱ ወቅታዊ የሀገር አድን ጥሪ በራሪ ወረቀት በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ በመገኘቱ ስጋት የገባው አሸባሪው የወያኔ ገዥ ቡድን የቤት ለቤት አሰሳ በማድረግ በአካባቢው ህብረተሰብ ላይ ወከባና እንግልት እያደረሰ እንደሚገኝ ከስፍራው የደረሰን የመረጃ ምንጭ ያስረዳል።
|
|
Read more...
|
|
|
|
|
|
|
Page 1 of 16 |